ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በሀዋሳና አካባቢው የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እየጎበኙ ነው

ግንቦት 10/2014 (ዋልታ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞና ካቢኔ አባላት በሀዋሳና አከባቢው የሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዲስትሪዎች እየጎበኙ ነው።
የመስክ ምልከታው የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ አካል ሲሆን በአሁን ሰዓት የታቦር ሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ የምርት ሂደትና የማስፋፊያ ፕሮጀክት ሥራ እየተጎበኘ ነው።
ውጤታማ አምራች ኢንዱስትሪዎች ልምዶቻቸውን በማስፋት የማምረት አቅምን ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬና ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።