በፀጥታ አካላት ሪፎርም ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

ግንቦት 11/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ ከምክክር፣ ጥናትና ትብብር ማዕከል ጋር ያዘጋጀው በፀጥታ አካላት ሪፎርም ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የፓናል ውይይቱ የፀጥታ አካላት ለውጥና የሲቪል ወታደራዊ ግንኙነት እንዲሁም የሰላም ማስከበር ዘመቻ ተግዳሮቶችና መልካም አጋጣሚዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡

የመከላከያ ኅብረት ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንንና የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ኃላፊ ብርጋዲየር ጀነራል ቡልቲ ታደሰ ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡

የፓናል ውይይቱን የምክክርና ጥናት ትብብር ማዕከል የቦርድ አባሉ አምባሳደር ተቀዳ አለሙ (ዶ/ር) በአወያይነት ያስጀመሩ ሲሆን ፖለቲከኛ ሌንጮ ለታ፣ የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ የጥናትና ምርምር ክፍል ኃላፊ ስራው ደማስ (ዶ/ር)፣ በመከላከያ ዋር ኮሌጅ የዓለም ዐቀፍና የአካባቢ ደኅንነት ጥናት ክፍል ኃላፊ ቃልአብ ታደሰ (ዶ/ር) ፓናሊስቶቹ ናቸው፡፡

በፓናል ውይይቱ ከፍተኛ ጀነራል መኮንኖች፣ የቀድሞ ጀነራሎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በሳሙኤል ሓጎስ