ኢትዮ ቴሌኮም ለተለያዩ ተቋማት የዳታ ማዕከል አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት እየተፈራረመ ነው

ግንቦት 12/2014 (ዋልታ) ኢትዮ ቴሌኮም ለተለያዩ ተቋማት የዳታ ማዕከል ወይም የዳታ ሴንተር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ስምምነት እየተፈራረመ ነው፡፡
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነቱን የተፈራረሙት ዘመን ባንክ ፣ ዘምዝም ባንክ ፣ ሂጅራ ባንክ ፣ ዌብስፕሪክስ እና ራይስ ማይክሮ ፋይናንስ ናቸው፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ከዚህ ቀደም ኢትዮ ቴሌኮም አይደለም ለሌሎች ተቋማት የዳታ አግልግሎት መስጠት ቀርቶ ለራሱም በቂ የዳታ ማዕከል አልነበረውም ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ግን ከራሱ አልፎ ለሌሎችም ለመትረፍ በቅቷል ብለዋል፡፡
በሜሮን መስፍን
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!