ክልሉ በሰላም ማስጠበቁ ረገድ አመርቂ ውጤት የሚታይበት መሆኑ ተገለጸ

ግንቦት 12/2014 (ዋልታ) በፌዴራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፖሊስን ጎበኝተዋል፡፡
ክልሉ በሰላም ማስጠበቁ ረገድ እጅግ አመርቂ ውጤት የሚታይበት መሆኑን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ ለሰላሙ መረጋገጥ የፌዴራል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ድጋፍ የጎላ እንደነበረ ጠቁመዋል፡፡
ተቋማቸው የክልሉን ፖሊስ ኮሚሽን በሎጀስቲክ፤ በቢሮ ቁሳቁስ እንዲሁም በስልጠና እንደሚደግፍም ቃል ገብተዋል፡፡
የደበብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ የፌዴራል ፖሊስ የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት እገዛ ሲያደርግ መቆየቱን መናገራቸውን የክልሉ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነትና ገጽታ ግንባታ መረጃ አመላክቷል፡፡
የክልሉ ፖሊስ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ በሚያደርገው እንቅስቃሴ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን አስረድተው አሁንም ሁለንተናዊ ሰላም በክልሉ እንዲሰፍን ለማስቻል ከክልሉ ፖሊስ ጎን በመሆን ድጋፉን አጠናከሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።