በድሬዳዋ ከተማ “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ

“ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ

ግንቦት 13/2014 (ዋልታ) “ስለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ በዛሬው እለት በድሬዳዋ ከተማ ተከፍቷል።

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀውን የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ የገንዝብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር መርቀው ከፍተውታል።

በአውደ ርዕዩም ከ1960ዎቹ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የተከናወኑ አበይት ኩነቶች የሚያስቃኙ ፎቶግራፎች ለእይታ ቀርበዋል።

የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ለሦስት ቀናት ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆንም ተገልጿል።

በእለቱም ከፎቶግራፉ አውደ ርዕይ በተጨማሪ “ኢትዮጵያ እያሸነፈች ትሻገራለች” በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ተስፋዬ ኃይሉ (ከድሬዳዋ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW