ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በበርሚንግሀም 5 ሺሕ ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ድል ቀናቸው

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች

ግንቦት 13/2014 (ዋልታ) የበርሚንግሀም ዳይመንድ ሊግ የ5 ሺሕ ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ድል ቀንቷቸዋል።

ትላንት በተካሄደው ውድድር ዳዊት ስዩም 14:47.55 ሰዓት በመግባት 1ኛ ስትወጣ፣ ሀዊ ፈይሳ 14:48.94 እና ፋንቱ ወርቁ ደግሞ 14:49.64 ሰአት ተከታትለው በመግባት 2ኛ እና 3ኛ ሆነው ውድድሩን እንዳጠናቀቁ የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!