ዳያስፖራው በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

ግንቦት 15/2014 (ዋልታ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ጉዳት ያደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት መልሶ ለመገንባት ዳያስፖራው እገዛ እንዲያደርግ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡

ሚኒስትሩ ጥሪውን ያቀረቡት በኢንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በለንደን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተመራማሪዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላይ ነው፡፡

በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር በሁሉም የትምህርት እርከን እየተካሄደ ያለው ማሻሻያ ለመጪው የኢትዮጵያ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዳያስፖራ ባለሙያዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

አክለውም የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ለሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውን በእንግሊዝ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW