80 ሺሕ ብር ጉቦ የተቀበለ የገቢዎች ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

ግንቦት 15/2014 (ዋልታ) ሃሰተኛ ደረሰኝ አቅርብሃል በሚል ምክንያት ከአንድ ግብር ከፋይ ላይ 80 ሺሕ ብር ጉቦ የተቀበለ የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የታክስ ኢንተለጀንስ ባለሙያ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ገቢዎች አነስተኛ ግብር ከፋይ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የታክስ ኢንተለጀንስ እና የኦፕሬሽን ባለሙያ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ መብታቸውን አውቀው ሙስናን በመጠየፍ ሙሰኞች በህግ እንዲጠየቁ የሚያደርጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥቆማቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲል ጥሪውን አቅርቧል፡፡