የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ እና አምባሳደሮች ጅግጅጋ ገቡ

ግንቦት 16/2014 (ዋልታ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ (ዶ/ር) ፣ የጣሊያን፣ ጃፓን ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ቼክሪፐብሊክ እና ፊንላንድ አምባሳደሮች እና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት፣ ዩኒሴፍ ፣ ፋኦና አይ ኦ ኤም ኃላፊዎች ጅግጅጋ ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑ ገራድ ዊል ዋል ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሁሴን ሀሺ ቃሲም (ዶ/ር) ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አያን አብዲና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ኃላፊዎቹ በጅግጅጋ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን መልሶ ማቋቋም በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል።