በ2030 የህፃናትን መቀንጨር ዜሮ ለማድረግ እየተሰራ ነው

ግንቦት 16/2014 (ዋልታ) በ2030 የህፃናትን መቀንጨር ዜሮ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በሰቆጣ ቃል ኪዳን ላይ ለደቡብ ክልል ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጃ ዱጉማ እንደተናገሩት የህፃናትን መቀንጨር በፈረንጆቹ 2030 ዜሮ ለማድረግ የ15 አመት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።
በሀገሪቱ በ37 ወረዳዎች የሚታየውን የልጅነት የምግብ እጥረት ችግር ለመፍታት የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተግባራዊ መደረጉንም ገልጸዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ 37 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት የዚህ ችግር ተጠቂ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው አመራሩ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ የድርሻውን እንዲወጣ መጠየቃቸውን የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።