ለ22ኛ ንስር እግረኛ ክፍለ ጦር ሰማዕታት የመታሰቢያ ሃውልት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

ግንቦት 18/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለ22ኛ ንስር እግረኛ ክፍለ ጦር ሰማዕታት የመታሰቢያ ሃውልት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ።

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት በክፍለ ጦሩ ግቢ እየተካሄደ በሚገኘው የሰራዊቱ እውቅና አሰጣጥ መርኃ ግብር ጎን ለጎን ነው።

ሃውልቱ የሚገነባው የክፍለ ጦሩ አባላት ለኢትዮጵያ ሰላም መጠበቅ የከፈሉትን መስዋእትነት ለመዘከር መሆኑን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ሠይፈ ኢንጊ በወቅቱ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ቤተ-መጻሕፍት እና ሌሎች ለሰራዊቱ የሚሆኑ የመዝናኛ ህንጻዎችን እንደሚያሚያካትት አዛዡ አስረድተዋል።

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመሰረት ድንጋዩን ካስቀመጡ በኋላ በክፍለ ጦሩ ግቢ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ማካሄዳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የክፍለ ጦሩን ሂደት የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርእይም በሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW