ጉባኤው በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በዶሃ ከፈተ

ግንቦት 19/2014 (ዋልታ) ዜጎች በአገራዊ ጉዳዮች ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ለማስቻል በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በኳታር ዶሃ መክፈቱን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጉባኤው በሰላም ግንባታ፣ በአብሮነት እና በመከባበር የጋራ ዕሴቶች ዙሪያ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ለዚህም አገራዊና ተቋማዊ ጥንካሬ እንዲፈጠር ከማስቻል አንፃር ከኢትዮጵያ ውጭ አራተኛውንና በአረቡ ዓለም የመጀመሪያውን ቅርንጫፍ በኳታር፣ ዶሃ መክፈቱን ነው ለኢዜአ የገለጹት።
ዶሃ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዳራሽ የሁሉንም ቤተ እምነት ከወከሉ የሃይማኖት አባቶችና በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር ፈይሰል አልይ በተገኙበት ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ በይፋ መከፈቱን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከዚህ ቀደም በሰሜን አሜሪካ፣ ኬኒያና ሮም ጣልያን የጉበኤውን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መክፈቱ ይታወሳል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!