ሀገር ዐቀፍ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ተጀመረ

ግንቦት 21/2014 (ዋልታ) የመጀመሪያው ሀገር ዐቀፍ የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት በሀዋሳ ከተማ ተጀመረ።

ለ15 ቀናት በሚቆየው በዚህ የኦሎምፒክ ውድድር ከሁሉም ክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ከ4 ሺሕ በላይ ስፖርተኞች በ15 የተለያዩ የውድድር ዘርፎች ተሳታፊ ይሆናሉ።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገር፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣  የዓለም የኦሎምፒክ አትሌቲክስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፖልተር ጋት እንዲሁም የክልልና የፌዴራል አመራሮች ተገኝተዋል።