ከንቲባ አዳነች የሕዝቡን ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነት እንሰራለን አሉ

ግንቦት 24/2014 (ዋልታ) የሕዝቡን አንገብጋቢ ችግር ለመፍታት ከመቸውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የ60 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የሕዝቡን አንገብጋቢ ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነት እንሰራለን፤ ሰርተንም እናስረክባለን ነው ያሉት፡፡