በሀገራዊ እረቀ ሰላም ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው

ግንቦት 25/2014 (ዋልታ) “ሰላም ለኢትዮጵያ” በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት አዘጋጅነት በሀገራዊ እረቀ ሰላምና ስምምነት ላይ የሃይማኖት አባቶች እየመከሩ ነው።

በሰላምና ግጭት አፈታት ዙሪያ የሃይማኖት ተቋማት እና የሃይማኖት አባቶች ሚና ላይ ነው ውይይት እየተካሄደ ያለው፡፡

ግጭቶች ተፈጥሯዊ ቢሆንም ግጭቶች የሚፈቱበት መንገድ በጥናትና ምርምር የታገዘ ባለመሆኑ በሀገሪቱ በርካታ ውድመቶች መኖራቸው ተገልጿል።

የግጭት አፈታት መንገድን ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ በመውሰድ ሕብረ-ብሔራዊነትን ማዳበር እንደሚቻል በመድረኩ ተነግሯል።

በማኅበረሰቡ ዘንድ አመኔታ ያላቸው የሃይማኖት አባቶች ግጭቶችን መፍታት ትኩረት የሚሰጡበት ተግባር መሆን አለበት ተብሏል።

በዙፋን አምባቸው