ልዑካኑ የጄህዲን የተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮሊየም የሥራ ሂደት እየተመለከተ ነው

ግንቦት 25/2014 (ዋልታ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ እና በገንዘብ ሚንስትር አህመድ ሺዴ የሚመራ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራር ልዑካን ቡድን ሶማሌ ክልል ገብተዋል።
ልዑኩ በሶማሌ ክልል ቆራሄይ ዞን ሽላቦ ወረዳ አከባቢዎች በሚገኘው ጄህዲን የተፈጥሮ ጋዝና ፔትሮሊየም ጉድጓዶች ሥራ ሂደት ለመመልከት ነው ወደ ክልሉ ያመሩት።
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማንና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ያካተተ ልዑካኑ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት ዋና አላማ የተፈጥሮ የነዳጅ ጉድጓዶች ቁፋሮና የነዳጅ ቧንቧዎች ዝርጋታ የሥራ ሂደትን መመልከት እንደሆነ የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።