4ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ጥናት ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው

ግንቦት 25/2014 (ዋልታ) 4ኛውን የፖሊስ ጥናት ሲምፖዚየም በሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እያተካሄደ ይገኛል።
በሲምፖዚየሙ ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ባለስልጣን እና የክልል ባለስልጣን ፣ ኮሚሽነሮች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው ብቃት ያላችውን የፖሊስ ባለሙያዎች ለማፍራት እንዲሁም እንደ ሀገር የተለያዩ ጥናት እና ምርምር ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት መስፍን አበበ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
በሲንፖዝየሙ 17 ጥናትና ምርምሮች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አራት የሚሆኑት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ሙሁራን የቀረቡ ናቸው።
ዩኒቨርስቲው ከሀገር ሰላም እና ፀጥታ ባልፈ የአፍሪካን ቀንድ ሰላም ለማስከበር እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል።
ይህም ሲምፖዚየም ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑ ታውቋል።
በቡላ ነዲ