ግንቦት 26 ቀን 2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሞጆ ከተማ አካባቢ እየተዘጋጀ ያለውን የኤክስፖርት አቮካዶ የችግኝ ጣቢያ እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤና በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጅጌን ጨምሮ የተለያዩ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና አመራሮች ተገኝተዋል ።
የተዳቀለ ኤክስፖርት አቮካዶ ከሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ በጉደቱ መስኖ ተጠቃሚዎች ህብረት ስራ ማህበር እየተዘጋጀ ይገኛል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።