ግንቦት 26/2014 (ዋልታ) 1 ሺሕ 85 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ 1 ሺሕ 85 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን እነዚህ ውስጥ ሁለት ህጻናትና 1 ሺሕ 83 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ 32 ሺሕ 321 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡