ርዕሰ መስተዳድሩ በቡታጅራ በ450 ሚሊየን ብር የተገነባ ሆስፒታል እና ሆቴል መርቀው ከፈቱ

ግንቦት 27/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳው በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ በ450 ሚሊየን ብር የተገነባውን የአለም ሆስፒታል እና የማቴዎስ መናፈሻ ሪዞርት ሆቴል መርቀው ከፈቱ።

የአለም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የማቴዎስ መናፈሻ ሪዞርት ሆቴል ዶ/ር ጸጋዬ ዘውዴ በተባሉ የግል ባለሃብት አማካኝነት ነው በ450 ሚሊየን ብር ግንባታው የተከናወነው።

ሆስፒታሉ ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስተር ተወካይ ዶ/ር አባስ ሀሰን፣ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ እንደሻው ሽብሩ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።