ዩኒቨርሲቲው ችግር ፈቺ አገልግሎቶችን በተጠናከር መልኩ እየሰጠ ነው ተባለ

ግንቦት 29/2014 (ዋልታ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰቡን ችግር መፍታት የሚያስችሉ ማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በተጠናከር መልኩ እየሰጠ እንደሚገኝ ጣሰው ወ/ሀና (ፕ/ር) ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘው የኢትየጵያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ 50ኛ አመት የምስረታ ክብረ በዓል ማጠቃለያ መርኃ ግብር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
በዚህ የማጠቃለያ መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ጣሰው ወ/ሀና (ፕ/ር) ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሰቲ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲወ ከመላው የአፍሪካ ሀገራት ስደስተኛ እንዲሁም ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ የሆነ ዩኒቨርስቲ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም የማኅበረሰቡን ችግር መፍታት የሚያስችሉ ማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን በተጠናከር መልኩ እየሰጠ እንደሚገኝ ነው የገለጹት።
የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ ላለፉት ሀምሳ አመታት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ቋንቋዎች እና ባህሎችን ከማስተዋወቅ እና ከማስደግ አንፃር አካዳሚው ያበረከተው አስተዋዖ ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል።
በሚኒስትር ማዕረግ የህግና ፍትህ ምርምር እና ስልጠና ተቋም ኃላፊ አምባሳደር ደግፌ ቡላ በበኩላቸው አካዳሚው በኢትዮጵያ ታሪክ በቋንቋ እና በባህል እድገት ውስጥ የኢትዮጽያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ አበርክቶ ከፍተኛ እንደነበር ገልጸው ይህንን አበርክቶውን አካዳሚው በቀጣይም አጠናክሮ እንዲቀጥል ነው መልዕክት ያስተላለፉት።

በሜሮን መስፍን