ቀዳማዊት እመቤቷ የስጋ ደዌ ተጠቂ ማኅበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት እድሳት አስጀመሩ

ግንቦት 29/2014 (ዋልታ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለሚኖሩ የስጋ ደዌ ተጠቂ ማኅበረሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት እድሳት አስጀመሩ፡፡

ከክረምት በፊት ተጠናቀው የሚያልቁ የስድስት አባዎራ ቤቶች እንደሚታደሱ ከቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የቤት እድሳቱ በማኅበረሰቡ ዘንድ የተዘነጉትን የስጋ ደዌ ተጠቂ ማኅበረሰብ አባላት ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የቤት እድሳቱ ተጨማሪ ተጠቃሚዎችን በማካተት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።