ከንቲባዋ በልደታ ክፍለ ከተማ አዲስ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን አስጀመሩ

የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ

ግንቦት 30/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ አዲስ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባዋ አጠቃላይ 36 ቤቶች ግንባታ ያስጀመሩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 28 የንግድ ቤቶች እና 8 መኖሪያ ቤቶች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

የሚገነቡ ሱቆቹና የመኖሪያ ቤቶች ወጣቶችንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል።

ግንባታው በአንድ ወር እንደሚጠናቀቅ እና ወጪውም በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እንደሚሸፈን ተጠቅሷል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የምንሰራቸውን የልማት ሥራዎች አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ለሚሰሩ የልማት ሥራዎች የባለሀብቶች ተሳትፎ የላቀ ነው ብለዋል፡፡

“ሁላችንም ዜጎች ተባብረን ለአንድ አላማ ከሰራን ሀገሪቱ የማትለወጥበት ምንም አይነት ምክንያት አይኖርም” ሲሉም መግለፃቸውን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ግንባታው ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበት የተገለጸ ሲሆን ቤቶቹ ሲጠናቀቁ አቅም ለሌላቸው ወገኖች እንደሚተላለፉ ታውቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW