አሜሪካ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚደረገውን የሰብዓዊ እርዳታ አደነቀች

ሰኔ 1/2014 (ዋልታ) አሜሪካ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን እንደምታደንቅ አስታወቀች።

በአንድ ሳምንት 1 ሺሕ 100 ተሽከርካሪዎች የተመጣጠነ ምግብ፣ የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁስ ይዘው ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱ የተባበሩት መንግሥታት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች ዓለም ዐቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች እያደረጉ ያለው ጥረትም የሚደነቅ መሆኑም በመግለጫው ተጠቁሟል።

ጅምሩን አጠናክሮ በማስቀጠልና እና በመነጋገር በዘላቂነት ግጭት እንዲቆም ማድረግ ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡