ኢዜማ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ

ሰኔ 1/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በጉባኤው የመጀመሪያ የኃላፊነት ግዜያቸውን ያጠናቀቁ የጉባኤ ተመራጭና ለጉባኤው በሚቀርብ የውሳኔ ሀሳብ አመራሮቹን ምርጫ እንደሚያካሄድ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረት በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የእጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 24 የሚያከናወን ይሆናል።

በዛሬው እለት የምረጡኝ ቅስቀሳቸው በይፋ የተጀመረ ሲሆን የብዙኃን መገናኛ አጠቃቀም የሰዓት ድልድልና የድምፅ መስጫ ካርድ አቀማመጥን ቅደም ተከተል መሰረት እጣ የማውጣት ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል።

የምረጡኝ ቅስቀሳ የፓርቲውን መተዳደሪያና ሥነ-ምግባር ደምብ እንዲሁም ሌሎች መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ የሚካሄድ ስለሆነም እጩዎች የሥነ-ምግባር መመሪያው ላይ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ማከናወኑን አቢሲ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW