ባንኩ በአዳማ ያስገነባውን ሕንፃ እያስመረቀ ነው

ሰኔ 2/2014 (ዋልታ) ኦሮሚያ ባንክ በአዳማ ከተማ ዲስትሪክት በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን ሕንፃ እያስመረቀ ነው።

ባንኩ በቀጣይም በሀገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሻራውን በማሳረፍ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎቶች ለደንበኞቹ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል።

ባንኩ ከሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ በማበደር ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱ ተነግሯል፡፡

ከዚህ ውስጥ ወደ 900 ሚሊየን ብር ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ፋይናንስ በማድረግ በሀገሪቱ ከሚገኙ የግል ባንኮች ቀዳሚ መሆኑም ተነስቷል።

ደረሰ አማረ (ከአዳማ)