በየካ ክፍለ ከተማ በአነስተኛ ዋጋ የቤቶች ግንባታ ተጀመረ

ሰኔ 2/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ቢሮ ከየካ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በአነስተኛ ዋጋ የቤቶች ግንባታን አስጀመረ፡፡

በዛሬው ዕለት የ10 የጂ+1 መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የማስጀመሪያ መርኃ ግብር የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ በክፍለ ከተማው ከ300 በላይ ቤቶች በአነስተኛ ዋጋ በመገንባት ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ለማስረከብ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ ያስሚን ውሃረቢ እና የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መራጊያው ተበጀ ግንባታውን አስጀምረዋል፡፡

በሳሙኤል ሓጎስ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW