ለባለሥልጣኑ አዲስ የሥራ አመራር የቦርድ አባላት ተሾሙ

ሰኔ 2/2014 (ዋልታ) ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ የሥራ አመራር የቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተሹመዋል።

ባለስልጣኑ ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጸሕፈት ቤት በተላከ ደብዳቤ አዲስ የሥራ አመራር የቦርድ አባላት እንደተመደበለት አስታውቋል።

በዚህም ፡-

? የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል – ሰብሳቢ

? የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) – አባል

? የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) – አባል

? የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋዬ ዳባ – አባል

?  የኢንፎርሜሽ መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) – አባል

? የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳህረላ አብዱላሂ – አባል

? የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተዶክተር አንዱዓለም አድማሴ አባልና ጸሀፊ ሆነው ተሸመዋል፡፡