የመንግሥት ሰራተኞች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

ሰኔ 12/2014 (ዋልታ) “እኔ የሕዝቤ አገልጋይ ነኝ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ አቀፍ የአመራር እና የሲቪል ሰራተኞች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስቀል አደባባይ ተካሄደ።
ዛሬ ማለዳ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የኢፌዴሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገኝተው በስፖርታዊ እንቅስቃሴው ላይ ተሣትፈዋል።
በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ በየክፍለ ከተማው የሚገኙ አመራሮች እና የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
በመርኃ ግብሩ ላይ የማርሻል አርት እና የብስክሌት ስፖርቶችም ተካሂደዋል።
የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመክፈቻው ላይ ባደረጉት ንግግር ብቁ እና ንቁ ሲቪል ሰርቫንት ለመፍጠር ስፖርት የዘወትር ልምዳችን ሊሆን ይገባል ብለዋል::
በመርኃ ግብሩ ላይ የአመራሮች የገመድ ጉተታ እና የሩጫ ውድድር ተካሂዷል።
በትዝታ ወንድሙ