ለሕዝባዊ ሠራዊቱ የዕውቅና መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

ሰኔ 12/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ ለሕዝባዊ የሠላም ሠራዊቱ በሰላምና ደኅንነት ላይ ላበረከተው አስዋጽኦ ለማመስገን የዕውቅና መርኃ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው።
በከተማ አስተዳደሩ ከ290 ሺሕ በላይ ሕዝባዊ ሠራዊት አባላት አሉ።
ሕዝባዊ ሠራዊቱ በኅልውና ትግሉ ወቅት ከሠራዊቱ ጋር በቅንጅት በመስራት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሚሰጥ እውቅና ነው።
በመርኃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ቀነዐ ያደታ ፣ የከተማው የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በሰለሞን በየነ