ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደኅንነትን መመለስ አሁንም ቅድሚያ የምንሰጠው ተግባራችን ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 13/2014 (ዋልታ) ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደኅንነትን መመለስ አሁንም ቅድሚያ የምንሰጠው ተግባራችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥ እና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት እና መተዳደሪያን ማውደም ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።

“ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤኒንሻንጉል እና ኦሮሚያ ክልሎች፣ ዋና ዓላማቸው ኅብረተሰቡን ማሸበር በሆነ አካላት የተፈጸመው የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊት የምንታገሰው አይደለም” ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።

ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደኅንነትን መመለስ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW