የቻይና-አፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 13/2014 (ዋልታ) የመጀመሪያው የሆነው የቻይና እና የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባዔው በአፍሪካ ቀንድ አገራት ሰላም፣ መልካም አስተዳደርና የልማት አጀንዳዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል ነው የተባለው።

ጉባዔው የቀንዱ አገራት አንድነት እንዲጠናከር፣ ለረጅም ጊዜያት ግጭትና ብጥብጥ ባልተለየው ቀጣና ሠላምና ልማት እንዲረጋገጥ ቻይና ከአገራቱ ጋር በጋራ ለመስራት ያላትን ፍላጎት ታላሚ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

የአፍሪካ ቀንድ አገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬኒያ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኤርትራ፣ ኡጋንዳ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳንን በአጠቃላይ 8 አገራትን ያጠቃለለ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ነው።

ቻይና በቀጣናው መጠነ ሰፊ ኢንቨስትመንት ያፈሰሰች ሲሆን አፍሪካን ከመካከለኛው ምስራቅ የሚያስተሳስረው የ“ሮድ ኤንድ ቤልት” ፕሮጀክትም ተጠቃሽ ነው።

በጉባዔው የቀንዱ አገራት እና የቻይና መንግሥት ልዑካን መታደማቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW