የኦሮሚያ ክልል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ሰኔ 13/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የገንዘብ ድጋፉን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አበርክቷል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዎጌሾ (ዶ/ር) የሁለቱ ክልል ሕዝቦች የተዛመዱ፣ አብሮ የመኖር ባህልን ያዳበሩና ወንድማማች መሆናቸውን አስታውሰዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ክልሉ 11ኛው ክልል ሆኖ ከተመሰረተ ወዲህ ክልሉን በመጎብኘት ከክልሎች የመጀመሪያው መሆናቸውንም ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትም ላደረገው የገንዘብ ድጋፍና ላሳየው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በበኩላቸው ነባር ክልሎች አዲስ የሚመሰረት ክልልን የመደገፍ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸው ለአዲሱ ክልል የተደረገው ድጋፍም በዚህ የሚያበቃ ሳይሆን ቀጣይነት የሚኖረው ነው ብለዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብትን የታዳለ እንደመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የመልማት እድል እንዳለውም ርዕሰሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል።

ነስረዲን ኑሩ (ከቦንጋ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW