1 ሺሕ 34 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

ከሳኡዲ አረቢያ ተመላሾች

ሰኔ 13/2014 (ዋልታ) 1 ሺሕ 34 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1 ሺሕ 34 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን እነዚህም አንድ ህጻንና 1 ሺሕ 33 ወንዶች መሆናቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል ነው የተባለው፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው 39 ሺሕ 887 ኢትዮጵያዊያንን መመለስ ተችሏል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW