ጉባኤው በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀሙ ግድያዎችን አወገዘ

ሰኔ 14/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰሞኑ በወለጋ፣ ጋምቤላ እና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀሙ ግድያዎችን አወገዘ፡፡

በሀገሪቱ የሚታየው የሃይማኖት ማንነትንና የብሔር ውግንናን መሠረት በማድረግ የሚፈፀመው ጥላቻ፣ ማፈናቀል፣ ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ፣ ግድያና ፍጅት እየተባባሰ ከመሄዱም በላይ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት እንደሆነ መቀጠሉ በእጅጉ የሚያሳስብ ነው ሲል ገልጿል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያዊያን መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር በማድረግ ሀገራዊ አንድነትን የሚሸረሽር የወንጀል ድርጊት እንደሆነ ጉባኤው አስገንዝቧል፡፡

በንፁኃን ላይ የተፈፀመው ግድያ ወንጀል ከመሆኑም በላይ ድርጊቱ ንፁሃንን የማሸበር ተግባር  መሆኑን ከኢኦቴቤ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

መንግሥት በዘላቂነት የሕዝቡን ደኅንነትና ሰላም የማስጠበቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጉባኤው ጠይቋል፡፡