ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሕግ ማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀመጠ

ሰኔ 15/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሕግ ማስከበር እርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ አስቀመጠ፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ኮሚቴው በስብሰባው በወቅታዊ ሀገራዊ የጸጥታ ጉዳይ እና እየተወሰደ ባለው የሕግ ማስከበር እርምጃ ላይ ተወያይቷል።

በዚህም አሸባሪ ቡድኖች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በንጹሃን ላይ የፈጸሟቸውን ግድያዎች አውግዟል።

የሽብር ቡድኖቹ ይህን የቀቢጸ ተስፋ ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት እየተወሰደባቸው ባለው ጠንካራ የሕግ ማስከበር እርምጃ የደረሰባቸውን ኪሳራ ለመሸሸግ መሆኑን ኮሚቴው ገምግሟል።

ሽብርተኞችን የመደምሰስ የሕግ ማስከበር እርምጃው ከዚህ ቀደም የጸጥታው ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቅጣጫ አስቀምጧል።

በአሁኑ ሰዓት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በተዛማጅ እና ሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ እንደሚገኝ የኢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW