ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ዐቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት ወሰነ

ሰኔ 15/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም ዐቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት መወሰኑን አስታወቀ።

የባንኩ የከረንሲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አበበ ሰንበቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታትና የኮንትሮባንድ ንግዱን ለመቆጣጠር ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከዓለም ዐቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ እንደ ወርቁ ብዛት ከ10 በመቶ እስከ 29 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ይገዛ እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህም ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ በነበሩት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሆነ የወርቅ አቅርቦት መገኘቱን ገልጸዋል።

በእነዚህ ዓመታት ባንኩ ከወርቅ ግብይት አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር አግኝቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡