አምባሳደር ሬድዋን ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ሰኔ 16/2014 (ዋልታ) የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊዊጂ ዲ ማዮ ጋር ተወያዩ።

አምባሳደር ሬድዋን ከሚኒስትሩ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በቀጣናዊ እና ዓለም ዐቀፍ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሊዊጂ ዲ ማዮ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር በማጠናከር በአውሮፓ ኅበረት በኩልም ሆነ በአንድ ወገን የምታደርገው ድጋፍ እንደምታስቀጥል ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የነበረው ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ሰብአዊ እርዳታን በማጎልበት፣ አካታች ብሔራዊ ውይይት እና ለሚስተዋለው ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሄ የመፈለግ እርምጃውንም አድንቀዋል።