በ2014 ዓ.ም በዲያስፖራው የተከናወኑ ሥራዎች እየተገመገሙ ነው

ሰኔ 18/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት በ2014 ዓ.ም በዲያስፖራው የተከናወኑ ሥራዎች እየገመገሙ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዳያስፖራው ከዚህ ቀደም ያከናወናቸው ጠንካራ ሀገራዊ ሥራዎች እና ስኬቶቻቸው ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
ውይይቱ በዋናነትም ዲያስፖራው ባለው አቅም ልክ በሀገሩ ጉዳይ ላይ እንዳይሰራ ክፍተት የፈጠሩ ችግሮች ምንድናቸው፤ ችግሮቹን እንዴት መቅረፍ ይቻላል የሚለው ጥያቄ ላይ ትኩረቱን አድርጓል።
በቀጣይም በሀገር ብሔራዊ ጥቅም ላይ የዲያስፖራውን ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ሥራዎችን ለመስራት ውይይት እየተደረገ ነው።
በ2015 ዓ.ም የኢትዮያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ፣ አዳዲስ ሀሰቦችን ለማፍለቅ እና የዲያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ በቀጣይ በልዩ ትኩረት የሚሰራባቸው ነጥቦች ተለይተው ለውይይት ቀርበዋል፡፡
በሜሮን መስፍን