በፌዴራል አስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ አተገባበር ላይ ግምገማ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 18 / 2014 (ዋልታ)  የፌዴራል አስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅን ተቋማት እንዴት እንደተገበሩት ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በጤና ሚኒስቴር፣ በገቢዎች ሚኒስቴር እና በጉምሩክ ኮሚሽን እንዴት እንደተተገበረ ክትትል ያደረገ መሆኑምኑ በግምገማ መድረኩ አመላክቷል፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ ስለ አዋጁ አተገባበር ማብራሪያ የሰጡት የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቃዱ ጸጋ የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ዜጎች መብትና ግዴታቸውን አውቀው ሀገራቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ አስተዋዕኦ አለው ማታቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው የፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ዜጎች የሚመሩበትን ህግ እንዲያውቁና አዳዲስ መመሪያዎች ሲወጡም ተሳትፎ በማሳደግ መብትና ግዴታቸውን እንዲለዩ ሚናው ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

በሀገር የአስተዳደር ተቋማት ላይ የዜጎችን መብት በሚገባ ለማረጋገጥ አዋጁ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ውይይቱ የተቋማቱ የአዋጁን አፈጻጸም በማየት፣ ክፍተታቸውን በመገምገም በቀጣይ የዜጎችን ተሳፎቶ ማሳደግ እንዲቻል የቤት ሥራ ይዘው የሚሄዱበት እንደሚሆንም ነው የተገለፀው።