የንግድ ባንክ የጎልፍ ውድድር ተጀመረ

ሰኔ 18/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2014 ዓ.ም የጎልፍ ውድድር ተጀመረ፡፡
ውድድሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ ጎልፍ ክለብ እና ከኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን በጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብ መከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ውድድሩ ለ2ኛ ጊዜ የሚከናወን ሲሆን 60 ተወዳዳሪዎች በተለያዩ የውድድር አይነቶች እየተሳተፉ ነው፡፡
የኢትጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ወጋየሁ ገ/ማሪያም፣ የኢትዮጵያ ጎልፍ አሶሴሽን አመራሮች እንዲሁም የኤፌድሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በመሰረት ተስፋዬ