በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 19 ሚሊየን ወጣቶች ይሳተፋሉ ተባለ

ሰኔ 20/2014 (ዋልታ) የ2014 የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ እና የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርኃ ግብር “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በዘንድሮ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት 19 ሚሊየን ወጣቶች በ12 የስምሪት መስኮች ይሳተፋሉ ብለዋል።

በዚህም 40 ሚሊዮን የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑና የ11 ቢሊየን ብር አገልግሎቶች ይሰጣሉ ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ፣ ማኅበረሰብ አቀፍ አግልግሎት፣ የሰላምና ደኅንነት ማስጠበቅ፣ ግብርና እና ሌሎችም መስኮችን አገልግሎቱ እንደሚያጠቃልልም ገልጸዋል፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የማስጀመሪያ መርኃ ግብር የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ታድመዋል።

በትዕግስት ዘላለም