በአዲስ አበባ 4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በይፋ ተጀመረ

4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር

ሰኔ 21/2014 (ዋልታ) “ዐሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ 4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች፣ የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም ሌሎች የፌዴራልና የከተማዋ ከፍተኛ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ26 ሚሊየን በላይ ችግኝ በመትከል ለአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ስኬት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸውም ተገልጿል።

በዛሬው እለት 30 ሺሕ ችግኞች ይተከላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW