አንጋፋው ፀሐፌ ተውኔት ሰለሞን አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ሰለሞን አለሙ

ሰኔ 21/2014 (ዋልታ) አንጋፋው ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅ እና ተዋናይ ሰለሞን አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በ”አብዬ ዘርጋው” የሬዲዮ ድራማ ይበልጥ የሚታወቀው ሰለሞን አለሙ በ5 ቋንቋዎች ከ500 በላይ የሬዲዮ ድራማዎችን፣ የመድረክ ቴአትሮችን እና መነባንቦችን ሰርቷል።

ለአብነትም ከዳንኪራው ጀርባ፣ ፍራሽ ሜዳ፣ ገመዱ እና አዙሪትን የመሳሰሉ ተወዳጅ ሥራዎች አበርክቷል።

በኢትዮጵያ ሬዲዮ ታሪክ በተለይ ከ1975 እስከ 1980 ገናና ሥራዎችን ያበረከተበት ወርቃማ ዘመኑ ነበር።

እንደኢብኮ ዘገባ ሰለሞን በቅርቡ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሌሊቱን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW