የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 22/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ 1ኛ ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ጉባኤው “የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በጉባኤው የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት መሰረት መስቀሌ፣ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ጥላሁን ከበደ፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፣ የክልል እና የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የደቡብ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽ ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡