የጄኔራል ዋቆ ጉቱ የመታሰብያ ሀውልት ተመረቀ

ሰኔ 22/2014 (ዋልታ) በኦሮሞ የትግል ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የጄኔራል ዋቆ ጉቱ የመታሰብያ ሀውልት ተመረቀ።

በሮቤ ከተማ በ22 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የመታሰብያ ሀውልት ለቱሪስት መስህብነት ሊውል በሚችል መልኩ የተገነባ መሆኑም ተነግሯል።

የመታሰብያ ሀውልቱን መርቀው የከፈቱት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ጀግኖች መስዋት የከፈሉት ለሕዝቦች ነፃነት እና እኩልነት ነው ብለዋል።

ለሕዝቦች ነፃነት እና እኩልነት መስዋት ከከፈሉት ውስጥ ጄኔራል ዋቆ ጉቱ እንደሚጠቀስ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ታሪክ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ታሪክ የሌለው ሰው ጀግና ሊኖረው እንደማችል የተናገሩ ሲሆን በብዙ ታሪክ ውስጥ ያለፈው የኦሮሞ ሕዝብ ነገም ብዙ የሚሰራቸው ታሪኮች እንደሚጠብቁትም አውስተዋል።

የዛሬ ትግላችን ሀገር መገንባት ነው ያሉ ርዕሰ መስተዳድርሩ በተለይም ኦሮሚያን የማልማት እንቅስቃሴ ገና ጅምር ላይ ነው ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እነ ጄኔራል ዋቆ ጉቱ የታገሉለት እና የተሰውለት ነፃነት ዳግም ወደ ኋላ እንዳይመለስ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

ሚልኪያስ አዱኛ (ከሮቤ)