ሚኒስቴሩ የአረንጓዴ አሻራ መረኃ ግብሩን በእንጦጦ ፓርክ አከናወነ

ሰኔ 24/2014 (ዋልታ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የ2014 አረንጓዴ አሻራ መረኃ ግብር በእንጦጦ ፓርክ አከናውነዋል፡፡

የችግኝ ተከላ መረኃ ግብሩን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ያስጀመሩት ሲሆን በእለቱም 10 ሺሕ ችግኞችን ለመትከል መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ችግኞች በተሟላ እንክብካቤ እንዲጸድቁ ሁሉም ተሳታፊዎች ቀጣይ የመንከባከብ ሥራ እንደሚጠበቅባቸው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ አስገንዝበዋል፡፡