በአዲስ አበባ በቀን 86 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ፕሮጀክት ነገ ይመረቃል

ሰኔ 25/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ በቀን 86 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውሃ ማምረት የሚችል ፕሮጀክት በነገው ዕለት በይፋ እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቱ 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በጀት ተመድቦለት የተገነባ የመጀመሪያው ትልቅ የከርሰ ምድር የውሃ ፕሮጀክት መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የግንባታ ወጪውም በከተማ አስተዳደሩ በጀት የተሸፈነ ሲሆን ፕሮጀክቱ ከ860 ሺሕ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW