ጠ/ሚ ዐቢይ መሰናክሎች የዕድገት እና የመሻሻል ዕድሎች ናቸው አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ሰኔ 27/2014 (ዋልታ) በመንገዳችን ላይ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ተቋቁመን ማለፍ ከቻልን መሰናክሎች የዕድገት እና የመሻሻል ዕድሎች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ባለፍንባቸው ጊዜያት ጎን ለጎን በጎ ነገሮችንም መፍጠር ችለናል ብለዋል።

የተለያዩ መሰናክሎችን በመቋቋም ጭምር በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች የጠንካራ ሥራ ውጤቶች ናቸው ሲሉም አክለዋል።

ፕሮጀክቶቹ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተሰነቀው ራዕይ ማሳያ ምልክቶች ናቸውም ነው ያሉት።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW