ከባንክ እንደተደወለ በማስመሰል የማጭበርበር ሙከራዎች እየተደረገ በመሆኑ ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ማሳሰቢያ ተሰጠ

ሰኔ 28/2014 (ዋልታ) አጭበርባሪዎች ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ በመሆኑ ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

አገልግሎቱ አጭበርባሪዎች የግለሰቦች ስልክ ላይ በመደወል እና ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ሽልማት ደርሷችኋል፣ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታችሁን አስተካክሉ እና ሌሎች መሰል መልእክቶችን በማስተላለፍ ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ እንደሆነ ጥቆማዎች ደርሰውኛል ብሏል።

ግለሰቦች እንደዚህ ዓይነት መልእክቶች በሚደርሳቸው ወቅት አቅራቢያቸው በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከማረጋገጣቸው በፊት ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመጠንቀቅ ራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ አሳስቧል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW